የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ሼር ካምፓኒ ሥራ አስክያጅ በአቶ ክፍሌ ወልዴ የሚመራው ልኡካን ቡድን በትናንትናው እለት በጅማ ከተማ በመገኘት ጅማ ከተማ የ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርለግን ለማዘጋጀት ባስገባቺው ጥያቄ መሰረት የመጀመሪያውን ዙር ግምገማ አከናውነዋል
በግምገማቸውም በከተማይቱ በመዘዋወር የዝግጅት እና ልምምድ ሜዳዎችን ሆቴሎችን እንዲሁም ዋነኛ የሆነውን የመጫወቻ ሜዳውን ግምገማ በማድረግ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት በግምገማቸውም ከተመለከቱት መስተካከል ያለባቸውን አንድአንድ ጉዳዮች በማሳወቅ ግምገማቸውን አጠናቀዋል።