የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ሲደረጉ በፀሎት ልዑልሰገድ ፣ አዳነ ግርማ እና ሳምሶን ሙሉጌታ በዲሲፕሊን ኮሚቴው እንዲቀረቡ ጥሪ ተላልፎላቸዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ዋና አሰልጣኝ በፀሎት ልዑል ሰገድ ዛሬ 10:00 ላይ በድሬዳዋ ስታድየም እንዲገኝ ሲል የዲሲፕሊን ኮሚቴው አሳውቋል።
እንዲሁም የቅዱስ ጊዮርጊስ ምክትል አሰልጣኝ ሳምሶን ሙሉጌታ እና የቡድን መሪው አዳነ ግርማ ደግሞ በመጪው ቅዳሜ 6:15 ላይ በድሬዳዋ ስታድየም እንዲገኙ ጥሪ ተላልፎላቸዋል።
በተጨማሪም የመቀሌ 70 እንደርታው መድኃኔ ብርሀኔም ዛሬ 10:30 ላይ በተመሳሳይ በድሬዳዋ ስታድየም እንዲገኝ ጥሪ ቀርቦለታል።
- ማሰታውቂያ -
በተያያዘም ሀዋሳ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ድቻ በሳምንቱ ጨዋታዎቻቸው አራት እና ከዛ በላይ የሆኑ ተጫዋቾቻቸው ካርዶችን በመመልከታቸው እያንዳንዳቸው ክለቦች የ5 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተወስኖባቸዋል።