ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 11ኛ ሳምንትና የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ !
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 11ኛ ሳምንት በተደረጉ ሰባት ጨዋታዎች አምስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ሁለት ጨዋታ በአቻ ሲጠናቀቁ 16 ጎሎች በ14 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። የጎሎቹ አገባብ ሁለት በፍፁም ቅጣት ምት ቀሪዎቹ በጨዋታ የተቆጠሩ ናቸው። በሳምንቱ 39 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ አንድ ተጫዋች በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ታህሳስ 01/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
በተጫዋች ተባረክ ሔፋሞ (ሃዋሳ ከተማ) ክለቡ ከ መቻል ጋር ባደረገው ጨዋታ በ77 ኛ ደቂቃ ላይ ከባድ የአጨዋወት ጥፋት ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል አቶ ጌታቸው ታዳሙ /የቡድን መሪ ወልቂጤ ከተማ / ክለቡ ከኢትዮጵያ መድን ጋር በነበረው የ11ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ቅድመ ስብሰባ ወቅት ከ15 ደቂቃ በላይ ዘግይተው ስለመምጣታቸው ሪፖርት የቀረበባቸዋል ለፈፀሙት ጥፋት ከለቡ በፕሪምየር ሊጉ የውድድር ደንብ መሰረት የቡድን መሪው ብር 1000/አንድ ሺህ/ እንዲከፍሉ ወስኗል።
- ማሰታውቂያ -
በክለቦች ሀዲያ ሆሳዕና በሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ አምስት ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል ሲወሰን ድሬዳዋ ከተማ ክለቡ ከፋሲል ከነማ ጋር በነበረው የ 11ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸውና የተቃራኒ ቡድን ተጫዋች ላይ ቁሳቁስ ስለመወርወራቸው ሪፖርት ቀርቦበት በዕለቱና ከዚህ በፊት የከለቡ ደጋፊዎች ተሳድበው በተቀጡት ቅጣት ሊታረሙ ባለመቻላቸው በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ብር ሰባ አምስት ሺህ / 75000/ እንዲሁም የተቃራኒ ቡድን ተጫዋች ላይ ቁሳቁስ በመወርውራቸው ብር 25000 /ሃያ አምስት ሺህ/ በድምሩ ብር የ100000 /አንድ መቶ ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል።