ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 የ7ኛ ሳምንት በተደረጉ አራት ተስተካካይ ጨዋታዎች ሶስቱ በመሸናነፍ አንድ ጨዋታ በአቻ ሲጠናቀቁ 12 ጎሎች በ10 ተጫዋች ተቆጥረዋል። በሁለቱ ቀን ጨዋታዎች 18 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ የተመዘገበ ቀይ ካርድ የለም።
የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ አርብ ታህሳስ 18 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
በተጫዋቾች ደጉ ደበበ(ወላይታ ድቻ) እና ግርማ በቀለ(ሀዲያ ሆሳዕና) በተለያዩ 5 የክለባቸው ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ በመመልከታቸው እያንዳንዳቸው በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል።