የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ በሊጉ አንደኛ ዙር ውጤት ለዋጭ ስህተት ሰርተዋል ያላቸውን ሶስት ረዳት ዳኞች ላይ የዕገዳ ውሳኔ አሳለፈ።
ከፌዴሬሽኑ ታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ ወልቂጤ ከተማ ከሲዳማ ቡና 0ለ0 በተለያዩበት ጨዋታ ወልቂጤ ያስቆጠረውን ግብ የሻረው ፌዴራል ረዳት ዳኛ ዳንኤል ጥበቡ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአርባምንጭ ባደረጉት ጨዋታ በተመሳሳይ የተቆጠረውን ግብ የሻረው ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ክንዴ ሙሴ እንዲሁም
ሰበታ ከተማ ከአርባምንጭ 1 ለ1 በተለያዩበት ጨዋታ ሰበታ ያስቆጠረውን ግብ የሻረው ፌዴራል ረዳት ዳኛ ደረጄ. እያንዳንዳቸው በስድስት ወር እንዲታገዱ ተወስኗል።
በቀጣይም ማስጠንቀቂያና ዕገዳ የሚተላለፍባቸው የመሃል ዳኞችና ኮሚሽነሮች መኖራቸውም የውስጥ አዋቂው መረጃ ያስረዳል። ብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሁለተኛ ዙር ላይ የዳኞች ውጤት ለዋጭ ስህተቶችን ለመቀነስ ከተቻለም ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ እንዲቻል የአቅም ማብቃት ስልጠና ለመስጠት ከፌዴሬሽኑ ጋር እየተዘጋጀበት መሆኑ ታውቋል።