የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ለ14ኛ ሳምንት የሊጉ መርሃግብር በዳኝነት የተመደቡትን 16 ዳኞች ይፋ አድርጓል።
በዚህ መሰረት በመሃል ዳኝነት የተመረጡት 10 ዳኞች ኢንተ.አርቢትር በዓምላክ ተሰማ፣ ኢንተ.አርቢትር ቴዎድሮስ ምትኩ፣ ኢንተ.አርቢትር ለማ ንጉሴ ፣ ፌዴራል አርቢትር ተካልኝ ለማ፣ ፌዴራል አርቢትር ባህሩ ተካ፣ ፌዴራል አርቢትር ተከተል ተሾመ፣ ፌዴራል አርቢትር ዮናስ ካሳሁንና
ፌዴራል አርቢትር ሄኖክ አበበ መሆናቸው ታውቋል።
በረዳት ዳኝነት የተመረጡት ደግሞ ኢንተ. ረዳት አርቢትር
ትግል ግዛው፣ ኢንተ. ረዳት አርቢትር ተመስገን ሳሙኤል፣
ኢንተ. ረዳት አርቢትር ሙስጠፋ መኪ፣ ፌዴራል .ረዳት አርቢትር አሸብር ታፈሰ፣ ፌዴራል ረዳት አርቢትር ኤፍሬም ሃ/ማሪያም፣ ፌዴ. ረዳት አርቢትር ሲራጅ ኑርበገን፣ ፌዴራል ረዳት አርቢትር ሙሉነህ በዳዳና ፌዴራል ረዳት አርቢትር ሸረፈዲን አልፈኪን መሆናቸው ታውቋል። 16ቱ አርቡትሮች ዛሬ ተጠቃለው ድሬዳዋ ይገባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን አወዳዳሪ አካሉ ከዳኞች ኮሚቴ ከተወከለው ባለሙያ ጋር በመሆን ከ16ቱ ዳኞች ጨዋታዎችን የሚመሩትን አርቢትሮች ይመድባሉ ተብሎም ይጠበቃል
ሊግ ኩባንያው ባወጣው መርሃግብር መሠረት ውድድሩ ነገ የሚቀጥል ሲሆን ከቀኑ 10 እና ከምሽቱ 1 ሰዓት ጨዋታዎቹ በድሬዳዋ የሚካሄዱ መሆናቸው ታውቋል። ሃሙስ ኢትዮጵያ መድን ከአዳማ ከተማ ድሬዳዋ ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ፣ ዓርብ ሀዋሳ ከተማ ከባህርዳር ከተማ ፋሲል ከነማ ከኢትዮ.ኤሌክትሪክ፣ ቅዳሜ ሲዳማ ቡና ከገጣፎ ለገዳዲ ቅ/ ጊዮርጊስ ከሀድያ ሆሳዕና ፣ እሁድ መቻል ከኢትዮጵያ.ቡና ወልቂጤ ከተማ ከወላይታ ድቻ ይጫወታሉ።