የ2015 ዓ.ም የውድድር ዘመን የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቀጣይ ጨዋታዎች የሚደረጉባቸው ስታዲየሞች በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርገዋል ።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ስራ አመራር ቦርድ የሶስት ከተሞችን(ባህር ዳር፣ አዳማ እና ሃዋሳ) ዝግጅት ከጎበኘ በኋላ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ቀጣይ የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች የሚደረግባቸውን ስታዲየሞች ለይቷል ።
ከአክሲዮን ማህበሩ በተላኩ ልኡካን ቡድኖችም የባህር ዳር ዩንቨርሲቲ ፣ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የሃዋሳ ዩነቨርስቲ ስታዲየሞች ተገምግመዋል ።
በዚህም መሰረት ከ17ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች እስከ 27ኛ ሳምንት ውድድሩ በቅደም ተከተል በመጀመሪያ በአዳማ ከተማ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እና በቀጣይ ደግሞ በሃዋሳ ከተማ በሃዋሳ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም እንዲደረጉ ተወስኗል ።
- ማሰታውቂያ -
የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2015 የወድድር ዘመን እስከ 17ኛው ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ድረስ በድሬደዋ ስታዲየም የተደረገ ሲሆን የ17ኛው ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎችና ከ18ኛ ሳምንት በኋላ ያሉ ጨዋታዎች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ መልስ የሚደረግ ይሆናል።