የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር አስቸኳይ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና የአንደኛው ዙር ግምገማ በዛሬው ዕለት በኢንተር ለግዠሪ ሆቴል ተካሂዷል ።
በጉባኤው በዋነኝነት አጀንዳ ሆነው የተነሱት የ2014 ዓመተ ምህረት የመጀመሪያ ዙር ውድድር ሪፖርት ግምገማ ፤ የኮቪድ 19 ቅድመ ምርመራ የተሻሻለውን መመሪያ ማፅደቅ ፤ የሊጉን ዋንጫ መተዳደራያ ደንብ ማፅደቅ ፤ የ2015 ዓመተ ምህረት የውድድር ዘመይ ክለቦች ለወድድር ለመመዝገብ ማማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ፤ የቦርድ አባላቶች ጥቅማ ጥቅቅ ክፍያ ማፅደቅ እና የአክሲዮን ማህበሩ የውጪ ኦዲት መሰየም ነበሩ ።
በአክስዮን ማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ በሆኑት መቶ አለቃ ፈቃደ የመክፈቻ ንግግር ከተደረገ በኋላ የሊጉ የአንደኛው ዙር ሪፖርቶች በሚመለከታቸው አካላት ቀርበዋል ።
በቅድሚያ የውድድር አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ሰብሳቢ በሆኑት ዶክተር ወገኔ ዋልተንጉስ ሲሆኑ በሁለቱም ከተሞች በተደረጉት ውድድሮች ላይ የተከወኑ ቅድመ ውድድር ተግባራት እና በውድድር ወቅት ያጋጠሙ ጉዳዮችን እና በሁለተኛው ዙር ሊስተካከሉ የሚገባቸው ነጥብችን ለመድረኩ አቅርበዋል ። በሪፖርቱ እንደ ጠንካራ ጎን ከተዘረዘሩት መካከል የሁለቱም ከተማ መስተዳድሮች ለውድድሩ የሰጡት ትኩረት ፤ ጨዋታዎች በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት እንዲከናወኑ ማድረግ ፤ የመጫወቻ ሜዳዎችን በሚቻለው መንገድ እንክብካቤ ማድረግ ፤ የዲሲፕሊን ግድፈት በፈፀሙ የቡድን አባላት ላይ በመመሪያው መሰረት የቅጣት ውሳኔዎች ማስተላለፍና እንዲተላለፉ ማድረግ ተጠቃሽ ናቸው የተባለ ። እንደ ክፍትት ከተገለፁት ውስጥ ደግሞ በዳኝነት ላይ አልፎ አልፎ የሚታዩ ክፍተቶች ፤ በጥቂት ኮሚሽነሮች ግምገማዎች የተጋነነ የዳኝነት ግምገማ መኖር ፤ የልምምድ ሜዳ ዕጥረት እና ክለቦች ፕሮግራም በወጣላቸው መሰረት ልምምዳቸውን ለማድረግ መቸገር ፤ የኮቪድ ምርመራ ክፍያ በወቅቱ አለመከፈል ፤ የጥቂት ክለቦች አመራሮች ለተስማሙበት ደንብና መመሪያ ተገዢ አለመሆን ከተነሱት ውስጥ ናቸው ።
በመቀጠል የአንደኛው ዙር ውድድር የዳኝነት ሪፖርት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ በሆኑት በአቶ ልዑልሰገድ በጋሻው የቀረበ ሲሆን በተለይም ከዳኞች አቅም ጋር በተያያዘ በሚነሱ ቅሬታዎች ላይ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን አስካሁን በስድስት ጨዋታዎች ላይ ውጤት ቀያሪ ስህተትፈቶች መፈፀማቸውን እና በ3 ዋና ዳኞች 6 ረዳት ዳኞች እና 1 የጨዋታ ኮሚሽነር ላይ የቅጣት ውሳኔ መተላለፉን በመግለፅ አፈፃፀማቸውን 90% ወይም በጣም ጥሩ ሲሉ የገለፁ ሲሆን በሚወሰኑ ቅጣቶች ላይ ግይ በቀጣይ ዕርምቶች ሊኖሩ እንደሚችል የገለፁ ገልፀዋል ።
- ማሰታውቂያ -
በመጨረሻ የቀረበው ሪፖርት ከህክምና ክፍል በመጡት ዶክተር ፍሬው አስራት አማካኝነት የቀረበ ሲሆን ከህክምና ክፍሎች መሟላት የቀይ መስቀል አገልግሎቶች ማደራጀት ጋር በተያያዘ እና ከኮቪድ ምርመራዎች ጋር በተያያዘ ገለፃ አድርገዋል ። በሪፖርታቸው እንደገለፁት ከኮቪድ ግር በተያያዘ በውድድሩ ከሚሳተፉ የክለብ አባላት 83% ያህሉ በሁለት ዙር የኮቪድ 19 ክትባትን የወሰዱ ሲሆን በአጠቃላይ 9,952 ምርመራዎች ተደርገው 59 የፖዘቲቭ ውጤቶች የተገኙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም 44 ተጫዋቾች መሆናቸውን ገልፀዋል ። በተጨማሪም ቀድሞ የነበረው የኮቪድ 19 ምርመራ አፈፃፀም መመራያ ተሻሽሎ መቅረቡ የተገለፀ ሲሆን ከሁለተኛው ዙር በኋላ ክለቦቹች ባረፉበት ሆቴል እየተዞረ የሚወሰደው የናሙና አሰባሰብ ተቀይሮ በስታድየሙ በሚዘጋጅ አንድ ስፍራ ላይ የምርመራ ናሙና እንደሚወሰድ እና ከዚህ ቀደም ከሚነሱ ጥያቄዎች በመነሳት አንድ ምርመራ የተደረገለት አባል ከጨዋታ 48 ሰዓት በፊት ምርመራ የማድረግ ግዴታ ያለበት ሲሆን ውጤቱ ፖዘቲቭ ሆኖ ድጋሚ ምርመራ ከጠየቀ ከጨዋታ መጀመሪያ ከ6 እስከ 18 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ሁለተኛ ምርመራ ማድረግ የሚችል ይሆናል ። በተያያዘም ዶክተር ፍሬው ያነሱት ከፀረ አበረታች ምርመራ ጋር የነበረውን አፈፃፀም ያቀረቡ ሲሆን ሁለት ተጫዋቾች የተከለከሉንጥረ ነገሮችን ተጠቅመው በመገኘታቸው እግድ እንደተጣለባቸው ተናግረዋል ።ሪፖርቶቹ ከቀረቡ በኋላ ከክለብ ተወካዮች ጥያቄዎች እና ምክረ ሀሳቦች ቀርበዋል ። ከተነሱት ጥያቄዎች መካከልም ክለቦቻቸው በውድድር ወቅት ካጋጠማቸው በመነሳት ሀሳቦቻቸውን ያነሱ ሲሆን ከተነሱት ሀሳቦች መካከልም ሰፊውን ሰአት የወሰደው ከዳኞች ጋር በተያያዘ የነበረው ሁኔታ ሲሆን ከክለቦች ከቀረቡ ቅሬታዎች በመነሳት በአቶ ልዑልሰገድ በጋሻው ግብረ መልሶች የተሰጡ ሲሆን በተጨማሪም በመቶ አለቃ ፈቃደ እንዲሁም በእርሳቸው ጋባዥነት በስፍራው በክብር እንግድነት ተገኝተው የነበሩት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አበበ ገላጋይ እና የፌዴሬሽኑ የፅህፈት ቤት ሀላፊ በሆኑት አቶ ባህሩ ጥላሁን አማካኝነት ከዳኞች ጋር በተያያዘ አስተያየት እና ተቋማቸው በጉዳዩ ላይ በቀጣይ ለመስራት ያሰባቸውን ነገሮች ለተሳታፊዎች አጠር አድርገው ተናግረዋል ።
በቀጣይም በሊግ አክስዮን ማህበር ስራ አስኪያጅ በሆኑት በአቶ ክፍሌ ሰይፈ አማካኝነት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ መተዳደሪያ ደንብ ፤ በቀጣይ የውድድር አመት የሚደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች በሜዳ እና ከሜዳ ውጪ እንዲደረጉ እንዲሁም ክለቦች የሚጫወቱባቸውን ስታድየሞች ለማስመዝገብ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ቀርበዋል ። ከዋንጫው ጋር ተያይዞ እንደገለፁት ዋንጫው ኢትዮጵያዊ ቅርፅ እንዲኖረው ሆኖ የተሰራ እንደሆነ እና በወገቡ ላይም ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ያስመዘገበቻቸው ቅርሶች ምስል እንዳረፈበት ገልፀዋል ። እንዲሁም የአሸናፊ ክለቦች ክለቦች ስም ከዋንጫው ስር እንደሚፃፍ እና የሊጉ አሸናፊ ክለብ ዋንጫው ከወሰደ በኋላ የቀጣይ የውድድር አመት ከመጀመሩ 10 ቀናት በፊት ዋናጫውን ለአክስዮን ማህበሩ ማስረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን የ100,000 ብር እና ከተቀመጠው ቀን ጀምሮ ዋንጫውን እስከሚመልስበት ዕለት የሚቆጠር ለእያንዳንዱ ቀን 10,000 ብር ተጨማሪ ቅጣት የሚጠብቀው ሲሆን ነገር ግን በቀጣይ 30 ቀናት ዋንጫውን ለመመለስ ካልቻለ እንደጠፋ ተቆጥሮ ዋንጫው የወጣበትን አስር እጥፍ ( 30 ሚሊየን ብር ) እንዲከፍል ይገደዳል ።
በተነሱት ሀሳቦች ላይ ሰፊ ውይይቶች እና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን ቀደም ብሎም በአፈፃፀም ሪፖትተላይደ እንደ ክፍትት የተነሳወሰ የደጋፊዎች በተጠበቀው ልክ ወደ ስታድየም ገብተው ጨዋታዎች ላለመልከታቸው የመግቢያ ዋጋ ከፍተኛ መሆን እንደምክንያት በመታየቱ ቅናሽ እንዲደረግበት ከውሳኔ የተደረሰ ሲሆን ( 300 ብር የነበረው 200 ብር ፤ 200 ብር የነበረው 100 ብር ፤ 100 ብር የነበረው 50 ብር ፤ 50 ብር የነበረው 20 ብር ) የውድድሩን ይዘት ወደ ቀድሞው ለመመለስ እና የስታድየሞች ምዝገባን በተመለከተ በጥልቀት ጥናት ተደርጎበት በቀጣይ ጉባኤ እንዲቀርብ ከስምምነት ላይ ተደርሷል ።