የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ሲያያቸው በነበሩ ሁለት ጉዳዮች ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ ወስኗል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ረቡዕ ሰኔ 29 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት በመመርመር እንዲሁም በኮሙኒኬ 30 ጥሪ የተደረገላቸው የጨዋታ አመራሮች እና የክለብ አባላት ጥሪ በማድረግ ካነጋገር በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
ድሬዳዋ እግር ኳስ ክለብ ክለቡ ከባህርዳር ጋር በነበረው የ28ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ግጥሚያው ከተጠናቀቀ በኋላ የክለቡ ደጋፊዎችና የቡድን አመራሮች አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበበት ሲሆን የክለቡ ደጋፊዎችና የቡድን አመራሮች በዕለቱ ባጠፉት ጥፋትና ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ጥፋት ከተቀጡት ቅጣትም ሊታረሙ ባለመቻላቸው ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 4 አንቀፅ 66 በተቁ 4(ሀ) መሰረት ብር 75000 /ሰባ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል ።
ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ክለቡ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በነበረው የ30ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ከ68ኛው ደቂቃ ጀምሮ ስፖርታዊ ጨዋነትን ያልተከተለ ድጋፍ ስለመስጠታቸው እና ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የጥበቃ ሃይሎች ሊቆጣጠሩት ባልቻለ ሁኔታ ወደ መጫወቻ ሜዳ ጥሰው ስለመግባታቸውና ስለማወካቸው እንዲሁም ለሜዳሊያ አስጣጥ ስነስርዓት አፈጻጸም እንቅፋት ስለመሆናቸው ሪፖርት ቀርቦበታል። በዚህም የክለቡ ደጋፊዎች በዕለቱ ባጠፉት ጥፋትና ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ጥፋት ከተቀጡት ቅጣት ሊታረሙ ባለመቻላቸው ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 3(ሀ) ና ለ(1) መሰረት ብር 100000 /አንድ መቶ ሺህ/ እንዲከፍልና በሜዳቸው የሚጫወቱትን ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች ያለደጋፊ በዝግ ስታዲየም እንዲያደርጉ ወስኗል።
- ማሰታውቂያ -
©Eplsc