– ሁለቱ ከተሞች ተፋጠዋል..…
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር መርሃግብር የሚካሄድበት ከተማና ስታዲየም ሃሙስ ምሽት ይታወቃል።
የሊግ ኩባንያው ገምጋሚ ቡድን ከፍተኛ ፍላጎት ያሳዩትን ሁለቱን ከተሞችና ስታዲየሞቹን ገምግሞ የአክሲዮን ማህበሩ የቦርድ አመራሮች የሚቀርብላቸውን የልዑኩን ሪፖርት ከመረመሩ በኋላ ከ15ቱ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች የተወሰነውን የሚያስተናግደውን ስታዲየም የሚመርጥ ይሆናል።
ውድድሩን በከተማው ማስተናገድ ከሚፈጠረው ድባብ በተጨማሪ የኢክኖሚ መነቃቃት የሚፈጥር የሆቴሎች የትራንስፖርትን ጨምሮ በርካታ ትርፎችን የሚያመጣ በዲ ኤስ ቲቪ መታየቱ የከተማውን ምቹነትና መልካም ምስል የሚያሳይ መሆኑ ፕሪሚየር ሊጉን ለማስተናገድ ክልሎቹ ጥያቄ ማቅረብ መጀመራቸው የሚያበረታታ መሆኑ የብዙዎችም እምነት ሆኗል።
- ማሰታውቂያ -
ድሬዳዋዎች ሰርተው ያጠናቀቁትን ሜዳ ለማሳየት አጋጣሚውን ለመጠቀም የጓጉ ሲሆን የከተማውን የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማጠናከር መዘጋጀታቸውን ዛሬ ለገምጋሚ ቡድኑ ያሳዩ ሲሆን ገምጋሚው ቡድን በነገው እለት ወደ ሀዋሳ ሄዶ ያለውን የዝግጅት ሂደት ከገመገመ በኋላ የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር የቦርድ አመራሮች ውሳኔያቸውን ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ገምጋሚው ቡድንና የቦርድ አመራሮቹ እግርኳሳዊ ባልሆነ ምክንያት ውሳኔያቸውን እንዳይቀለብሱ የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል።
የፕሪሚየር ሊጉ 1ኛ ዙር ከሃሙስ እስከ ቅዳሜ በሚደረጉ 8 ጨዋታዎች የሚጠናቀቅ ሲሆን መቻል በ30 ነጥብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ29 ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና በእኩል 25 ነጥቦች በግብ ክፍያ ተበላልጠው ከ1-4 ያለውን ደረጃ ይዘዋል።