ከ16ቱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር አባል ክለቦች የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊግ ኩባንያን መግለጫ በይፋ ተቃውሟል።
ክለቡ ጉዳዩን በተመለከተ ለአክሲዮን ማህበሩ በላከው ደብዳቤ “የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዝዳንታዊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫን በተመለከተ የሰጠውን መግለጫ መከታተሉን በመግለጽ ማህበሩ ከተቋቋመበት ዓላማ ከተሰጠው ተግባርና ሀላፊነት ውጪ የሰጠውን መግለጫ ተገቢነነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም”ሲል ኮንኗል።
“ምርጫው ሀገራዊ ጉዳይ እንደመሆኑ አክሲዮን ማህበሩ ባለድርሻ የሆኑትን 16ቱን ክለቦች ጠርቶ ማወያየት ይገባው ነበር” ያለው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ
” መግለጫው ምርጫው በፍትሀዊነት እንዳይካሄድ ተጽዕኖ እንዳይፈጥር ስጋት የገባን ሲሆን እንደ ክለብ የተሰጠውን መግለጫ አንቀበልም” ብሏል።
- ማሰታውቂያ -
ከሊግ ኩባንያው መግለጫ በፊት ወልቂጤ ከተማ፣ ሀድያ ሆሳዕና፣ አዳማ ከተማና ሰበታ ከተማ ከመግለጫው በኋላ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ የአክሲዮን ማህበሩን አቋም ተቃውመዋል።