የ2016 ዓመተ ምህረት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባሳለፍነው እሁድ ሲጀመር በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና በኤርሚያስ ሹምበዛ ብቸኛ ግብ 1 – 0 ማሸነፉ ይታወሳል ።
በጨዋታው ጉዳት አስተናግዶ ተቀይሮ የወጣው ግብ ጠባቂው በረከት አማረ ጉዳተለ ከበድ ያለ ቢመሰልም በነገው ዕለት ወደ ልምምድ እንደሚመለስ ክለቡ ይፋ አድርጓል ።
በተመሳሳይም በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጉዳት አስተናግዶ የነበረው ተከላካዩ ራምኬል ጀምስ መጠነኛ ልምምድ ማድረግ ጀምሯል ። በተመሳሳይ በጉዳት ከቡድኑ ተለይቶ የነበረው ሬድዋን ናስር ቡድኑን ተቀላቅሎ መጠነኛ ልምምድ ማድረግ ጀምሯል።
- ማሰታውቂያ -
በተለያዩ ምክንያቶች ከቡድኑ ጋር ልምምድ ያላደረገው አማካኙ አማኑኤል ዮሐንስ መስከረም 29/2016 ዓ.ም ሙሉ የልምምድ ዝግጅቱን የሚያጠናቅቅ በመሆኑ ቡድኑን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል ።
በተመሳሳይ መሐመድኑር ናስር ከሶስት ሳምንት በኋላ ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም እንዲሁም አብዱልሐቪዝ ቶፊቅ መስከረም 27/2016 ዓ.ም በተመሳሳይ የተያዘላቸውን የልምምድ ጊዜ እንዳጠናቀቁ ለውድድሩ ብቁ ሆነው ቡድኑን እንሚቀላቀሉ ተገልጿል ።