በአሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ የሚመራው ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ ቡና የቀድሞ የክለቡን ተጫዋች ኢያሱ ታምሩን ጨምሮ ሶስት ተጫዋቾችን አስፈርሟል።
በኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ተወዳጅ የሆነው እያሱ ታምሩ በሀድያ ሆሳዕና ካሳለፋቸው ሁለት የውድድር ዘመናት በኋላ ያለ ክለብ ቆይቶ ዳግም ቡናማዎቹ በአንድ አመት ውል ተቀላቅሏል።
በተጨማሪም ረጂብ ሚፍታህ(ለሁለት አመታት) ከባህርዳር ከተማ እንዲሁም ኪሩቤል ደሳለኝ(ለአንድ አመት) ከፋሲል ከነማ ጋር በመለያየት ለኢትዮጵያ ቡና ፊርማቸውን ያኖሩ ተጫዋቾች ናቸው።
ቡድኑ በተጨማሪም ከ20 አመት በታች ቡድኑ አራት ተጫዋቾችን(ተከተል በዙ ፣ ሀምዛ ሱልጣን ፣ ተመስገን ታደሰ እና ሁዛይፍ ረሺድ) በቢጫ ቴሴራ ለማጫወት ያስፈረመ ሲሆን እያንዳንዳቸው የአምስት አመታት ውልን ፈርመዋል።
- ማሰታውቂያ -
ኢትዮጵያ ቡና የውድድር ዓመቱን ቀዳሚ ጨዋታ ነገ ምሽት 1:00 ጀምሮ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያደርጋል።