ኢትዮጵያ ቡና ውጤታማ አልሆነም በሚል ከአሰልጣኝ ተመስገን ዳና ጋር መለያየቱ ይፋ ሆኗል።
አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ቡድኑን ውጤታማ እንደሚያደርግ ቃል ቢገባም የተመዘገበው ውጤት በዝውውሩ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉትን የኢትዮጵያ ቡና አመራሮችን ያስደሰተ አልሆነም። በዘንድሮ የውድድር አመት ባደረጋቸው 10 ጨዋታዎች በአራቱ አሸንፎ በተመሳሳይ በአራቱ ተሸንፎ ሁለት ጨዋታ ብቻ አቻ የወጣው አሰልጣኙ በተለይ በሀድያ ሆሳዕና 1ለ0 መሸነፉ ለስንብቱ ትልቁን ሚና መጫወቱ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ቡና የዛሬ 12 ቀን ከአዳማ ከተማ ጋር ቀሪ ጨዋታውን የሚያደርግ ሲሆን በ12ኛው ሳምንት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ወደ አዳማ ከተማ በመዞሩ ከተስተካካይ ጨዋታው በኋላ በ13ኛ ሳምንት ከኢትዮጵያ መድን ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በማከናወን ለቻን ውድድር ዝግጅት ውድድሩ ሲቋረጥ በቂ የማገገሚያ ጊዜ እንደሚኖረው ተገምቷል። ከድሬዳዋ ባገኘሁት መረጃ ደግሞ አሰልጣኙ ከክለቡ በመሰናበቱ ከክለቡ ሆቴል በመልቀቅ ወደ ኤርፖርቴት እየሄደ መሆኑ ታውቋል።
አመራሮቹ በቀጣዩ 11 ቀን አዲሱን አሰልጣኝ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የውጪ ሀገር አሰልጣኝና የአገር ውስጥ አሰልጣኞችን በማነጋገር ስራ ላይ መጠመዳቸውም እየተነገረ ነው።
- ማሰታውቂያ -
በእስካሁኑ የአስረኛ ሳምንት ውጤት መሠረት ኢትዮጵያ ቡና በ14.ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ 9ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።