*…ሀበሻ ቢራ 18 ሚሊየን ብር ለ2014 ይከፍላል ተብሏል
ኢትዮጵያ ቡናና ሀበሻ ቢራ ጋር ለቀጣዮቹ 5 አመታት አብረው ለመስራት ተስማሙ
ከነሀሴ 1/2013_ሰኔ 30/2014 ድረስ ባለው ውል መሠረት ሀበሻ ቢራ 18 ሚሊየን ብር ይከፍላል። ለዋናው ቡድን ለሴቶችና ለተስፋ በድን ማሊያ 4.5 ሚሊየን ብር ይከፍላል።ለክለቡ የሩጫ ውድድርም3.75 ሚሊዮን ብር፣ ክለቡና ሀበሻ ቢራ በጋራ በአመት ውሰጥ አራት ኤቨንት የሚዘጋጅ ሲሆን በእያንዳንዱ ኤቨንት 500ሺህ ብር ይከፍላል።ክለቡ ሊገዛ ላሰበው ዘመናዊ ሰርቪስ 12ሚሊዮን ብር ድጋፍ ይሰጣልም ተብሏል። ክለቡ ሻምፒዮን ከሆነ 2.7ሚሊየን ብር ማበረታቻ የሚሰጥ ሲሆን 2ኛ ከሆነ 900ሺህ ብር ይከፍላል። ሀበሻ ቢራ ከዚህም ውጪ ከ6_8ሺህ ብር ኢንሴንቲቭ ለመክፈልም ተስማምቷል።
በሁለቱ ወገኖች ስምምነት መሠረት የውሉ ተፈጻሚነት በ2014 እና 2015 የሚቀጥል ሲሆን ከ2016 ጀምሮ ውሉ እንደገና የሚታይ ይሆናልም ተብሏል። ሀበሻ ቢራም ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በቀጣዮቹ 5 አመታት ብቻ ሳይሆን ረጅም ጊዜ አብሮ የመቀጠል እቅድ እንዳለው ገልጾ በገበያው ላይ የተፈጠረ ችግር እንኳ ከክለቡ ጋር አብሮ እንደሚወጣው ርግጠኛ መሆኑን አስረድቷል።