አሰልጣኝ ተመስገን ዳናን በዋና አሰልጣኝነት ለመሾም ከስምምነት ከደረሱ ኋላ በዝዉዉር ገበያዉ ላይ በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች አሁን ደግሞ ወጣቱን የፊት መስመር ተጫዋች ብሩክ በየነን አምስተኛ ፈራሚ በማድረግ ወደ ስብስባቸዉ መቀላቀላቸው ተረጋግጧል።
ከዚህ ቀደም ለወልቂጤ ከተማ እንዲሁም ያለፉትን አራት አመታት ደግሞ ለሀዋሳ ከተማ መጫዎት የቻለዉ ተጫዋቹ በዘንድሮዉ የዉድድር አመት 14 ግቦችን ማስቆጠር ችሎ እንደነበርም ይታወሳል። በዚህም ወሳኝ አጥቂያቸዉ የነበረዉን አቡበከር ናስርን ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሸኙት ቡናማዎቹ ጥሩ ተተኪ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።