ሀምሌ 1 በይፋ በተከፈተዉ የተጫዋቾች የዝዉዉር መስኮት በንቃት በመሳተፍ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ በመቀላቀል ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች አሁን ደግሞ ስድስተኛ ፈራሚ በማድረግ ወጣቱን የአጥቂ አማካይ ስፍራ ተጫዋች አብዱልከሪም ወርቁን ማስፈረማቸዉ ዕርግጥ ሆኗል።
ያለፉትን ሁለት አመታት በክትፎዎቹ ቤት ድንቅ ጊዜን ማሳለፍ የቻለዉ ወጣቱ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አብዱልከሪም ወርቁ በሁለት አመት የኮንትራት ዉል ወደ ኢትዮጵያ ቡና ማምራቱ በዛሬዉ ዕለት ተረጋግጧል።