አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸዉ በመቀላቀል ላይ እና የነባር ተጫዋቾቻቸውን ዉል በማደስ ላይ የሚገኙት ቡናማዎቹ አሁን ደግሞ የወሳኙን የመስመር ተከላካይ ዉል ለሶስት አመት ማራዘማቸዉ ታዉቋል።
ለተጨማሪ ዓመት ውሉን ያደሰው አሥራት ቱንጆ በ2010 አመት ቡድኑን ኢትዮጵያ ቡናን ከተቀላቀለ በኋላ ከዓመት ዓመት የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች እየሆነ መምጣቱ ይታወቃል። ወደ ቡና ሲመጣ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የነበረው አስራት መስመር ተከላካይ ተቀይሮ እጅግ ጥሩ ብቃቱን ሲያሳይ መቆየቱም ይታወሳል።
በአሁኑ ሰአት ከኢትዮጵያ 23 አመት በታች ቡድን ጋር በባህርዳር የሚገኘዉ የዋልያዎቹ ወሳኝ ተጫዋች አስራት ቱንጆ ከክለቡ ኢትዮጵያ ቡና ጋር የሚያቆዉን ተጨማሪ የሶስት አመት የዉል ስምምነት መፈረሙ ተረጋግጧል።