የ2014 ዓመተ ምህረት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር በትላንትናው ዕለት መጠናቀቁ ይታወሳል ። በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ በ20 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ የሚመራው ኢትዮጵያ ቡና ለሁለተኛው ዙር ራሱን ለማጠናከር የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በዝውውሩ መክፈቻ ቀን የጀመረ ሲሆን የመጀመሪያው ፈራሚውንም ተመስገን ገብረ ኪዳንን አድርጓል ።ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ ሰበታ ከተማ ፣ ጅማ አባጅፋር ፣ መከላከያ የተጫወተ ሲሆን በቡናማዎቹ ቤትም ለሶስት አመታት የሚያቆየውን ኮንትራት ተፈራርሟል ።
ኢትዮጵያ ቡና ተመስገን ገብረኪዳን አስፈርሟል
![](https://i0.wp.com/www.hatricksport.net/wp-content/uploads/2022/03/PicsArt_03-03-03.55.23.jpg?resize=860%2C573&ssl=1)
Writer at Hatricksport