በዝውውር ገበያዉ ላይ በንቃት በመሳተፍ ሶስት ያህል ተጫዋቾችን በቶሎ ማስፈረም የቻሉት ኢትዮጵያ ቡናዎች ዛሬ ደግሞ ወጣቱን አጥቂ ተጫዋች ከሀዋሳ ከተማ ወደ ስብስባቸዉ መቀላቀላቸው ተረጋግጧል።
ከሀዋሳ ከተማ ታዳጊ ቡድን የተገኘዉ እና ለአመታት ለዋናዉ ቡድን በድንቅ ብቃት መጫወት የቻለዉ የመስመር አጥቂዉ መስፍን ታፈሰ በቅርቡ ወሳኝ አጥቂያቸዉን አቡበከር ናስርን ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሸኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች ቀጣዮቹን ሁለት አመታት ለመጫወት ፊርማውን ማኖሩ ታዉቋል።
በተያያዘም አሰልጣኝ ተመስገን ዳናን በዋና አሰልጣኝነት የሾሙት ኢትዮጵያ ቡናዎች በቀጣይ ቀናትም ራሳቸዉን ይበልጥ ለማጠናከር በዝዉዉር ገበያዉ ላይ በንቃት እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።