ኢትዮዽያ ቡና ዛሬ በተከፈተው የዝውውር መስኮት ጠንካራ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምሯል።
ከሰአታት በፊት በተገኘ መረጃ የሰበታ ከተማው ፉአድ ፈረጃና የጅማ አባጅፋሩና የቀድሞ ግብ ጠባቂ በረከት ጋር መስማማታቸው ታውቋል። በረከት ከጅማ አባጅፋር በፊት ለኢትዮዽያ ቡና የተጫወተ መሆኑ ወደ ቤቱ የመመለስ ያህል ተድርጎ ተነግሯል። ሁለቱ ተጨዋቾች እስከ ሰኞ ድረስ ሙሉ በሙሉ የካሳዬ አራጌን ስብስብ እንደሚቀላቀሉ ታውቋል። ተክለ ማርያም ሻንቆ ጋር መግባባት ያልቻለው ኢትዮዽያ ቡና ፈጣን በሆነ ሁኔታ ተተኪውን በረከትን ለማስፈረም ተስማምተዋል።
ኢትዮዽያ ቡና ከሁለቱ ተጨዋቾች ውጪ ስንታየሁ መንግስቱ ከወላይታ ድቻ ፣ ሰለሞን ሃብቴን ከመከላከያ ፣ መሳይ ዻውሎስን ከሰበታ ፣ቴዎድሮስ /ባርያውን/ ከሀድያ ሆሳዕና ለማስፈረም እየተደራደረ መሆኑ ተሰምቷል። በቀጣይ ቀናት ሌሎች ተጨዋቾች ለቡናማዎቹ ፊርማቸውን ያኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮዽያ ቡና ከተክለማርያም ሻንቆና አስራት ቱንጆ ሌላ ከኢያሱ ታምሩ፣ አዲስ ፍሰሃ ፍቅረየሱስ /ችምስ/ እንደማይቀጥሉና በ2014 በኢትዮዽያ ቡና ማሊያ እንደማይታዩ ታውቋል።