ኢትዮጵያ ቡናዎች የተከላካይ ክፍላቸዉን ይበልጥ ለማጠናከር ይረዳቸው ዘንድ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች እና ዘንድሮ ከግማሽ የዉድድር አመት በኋላ በጅማ አባጅፋር ያሳለፈዉን አንጋፋዉን የመስመር ተከላካይ ስዩም ተስፋየን ማስፈረማቸዉ ይታወሳል።
አሁን ደግሞ በመከላከያ፣በአዳማ፣በሀዲያ ሆሳዕና እና በሰበታ ተጫዉቶ ማሰለፍ የቻለዉን ተከላካዩን ቴዎድሮስ በቀለን በሶስት ዓመት ኮንትራት ዉል ማስፈረማቸዉ ተሰምቷል፡፡
በተያያዘም የአጥቂው አቡበከር ናስር ታናሽ ወንድም የሆነዉ ሬድዋን ናስር ከክለቡ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ለሶስት ዓመታት የሚያቆየውን ኮንትራት ፈርሟል፡፡
ባሳለፍነዉ የዉድድር ዓመት በመሃል ሜዳ እንቅስቃሴው የበርካቶችን ትኩረት የሳበው ሬድዋን ናስርን ለሶስት ዓመታት ከቡና ጋር የሚያቆየውን የውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
- ማሰታውቂያ -
አማካኙ ሬድዋን በኢትዮጵያ ቡናም ሆነ በሀገር ደረጃ ተስፋ ከሚጣልባቸው ወጣት ተጨዋቾች መካከል አንዱ ሲሆን፤ ሀገሩን በመወከል በሴካፋ ዉድድር ላይ ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ ይገኝ የነበረዉ አማካኙ ባገጠመዉ ጉዳት ምክንያት ከአሰልጣኝ ዉበቱ አባተ ስብስብ ዉስጥ ሊቀነስ ችሏል ፡፡