👉ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሴቶች 10 ሺህ ሜትር
👉ኢትዮጵያ እና የሴቶች 10 ሺህ ሜትር
ኢትዮጵያ በሩጫ ውድድሮች ላይ ደጋግማ ስኬታማ ከሆነችባቸው እና ሜዳልያዎትን ከሰበሰበችባቸው ውድድሮች መካከል አንደለ የሴቶች የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ነው ።
በአለም ሻምፕዮናዎችም ሆነ በኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ በመድረኩ እንደ እነ ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፤ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ፤ ኮማንደር አትሌት ጌጤ ዋሚ ፤ አትሌት መሰረት ደፋር ፤ አትሌት ብርሀኔ አደሬ ፤ ወርቅነሽ ኪዳኔ የመሳሰሉ አትሌቶች ለኢትዮጵያ የወርቅ ፤ የብር እንዲሁም የነሀስ ሜዳልያዎች ማስገኘት ችለዋል ።
- ማሰታውቂያ -
ኢትዮጵያ በእስካሁን የአለም አትሌቲክስ የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ላይ 7 የወርቅ ፤ 7 የብር እና 5 የብር ሜዳልያዎችን ማግኘት ችላለች ።
በመድረኩ የመጀመሪያ ሜዳልያ የተመዘገበው በአትሌት ደራርቱ ቱሉ አማካኝነት ሲሆን እ.ኤ.አ በ1995 ስዊድን ጎተንበርግ ላይ በተደረገው የአምስተኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ላይ የሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳልያ ማግኘት ችላለች ።
የመጀመሪያው ወርቅ ሜዳልያ ደግሞ በኮማንደር አትሌት ጌጤ ዋሚ የተገኘ ሲሆን እ.ኤ.አ በ1999 በስፔን ሲቪያ ላይ በተዘጋጀው 7ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ላይ ቀዳሚ ሆና በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ አስመዝግባለች ።
የወርቅ ሜዳልያዎች
1. ኮማንደር ጌጤ ዋሚ ( 1999 )
2. ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ( 2001 )
3. አትሌት ብርሀኔ አደሬ ( 2003 )
4. አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ( 2005 )
5. አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ( 2007 )
6. አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ( 2013 )
7. አትሌት አልማዝ አያና ( 2017 )
የብር ሜዳልያዎች
1. ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ( 1995 )
2. አትሌት ብርሀኔ አደሬ ( 2001 )
3. አትሌት ወርቅነሽ ኪዳኔ ( 2003 )
4. አትሌት ብርሀኔ አደሬ ( 2005 )
5. አትሌት መሰለች መልካሙ ( 2009 )
6. አትሌት ገለቴ ቡርቃ ( 2015 )
7. አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ( 2017 )
የነሀስ ሜዳልያዎች
1.ኮማንደር አትሌት ጌጤ ዋሚ ( 2001 )
2. አትሌት እጅጋየሁ ዲባባ ( 2005 )
3. አትሌት ውዴ አያሌው ( 2009 )
4. አትሌት በላይነሽ ኦልጅራ ( 2013 )
5. አትሌት ለተሰንበት ግደይ ( 2019 )