ደደቢት ባገዳቸው ሶስት ተጨዋቾች ማለትም በሳምሶን ጥላሁን ፤ ዳዊትፍቃዱ እና አክሊሉ አየነው ላይ ለፌዴሬሽኑ ይግባኝ አስገባ:: ተጨዋቾቹ በበኩላቸው ለክለቡ ያስገባነው የይቅርታ ደብዳቤ ከአንድ ወር በላይ ስለቆየ ወደ ፌዴሬሽኑ ሄደን ያቀረብነው ጥያቄ ፍትሀዊ ምላሽ በማግኘቱ ደስተኞች ነን ሲሉ ለሀትሪክ ስፖርት ድረ ገፅ ገልፀዋል ::
አቶ ተስፋዬ የደደቢት የሴቶች እግር ኳስ ክለብ የቡድን መሪ ከሀትሪክ ስፖርት ድህረገፅ ጋር ቆይታ አድርገዋል
አቶ ተስፋዬ ፡-ተጫዋቾች የገንዘብ ጥያቄ ጠይቀዋል በጥያቄያቸው መሠረት ሂሳባቸው ሲሰራ እንዳውም እላፊ ገንዘብ መውሰዳቸውን አረጋግጠናል፡፡
ተጫዋቾች ቀድመው ከደሞዛችን እሚቆረጥ ግማሽ ክፍያ እያሉ እንደሚወስዱ በኛም በብዙ ክለቦች ይታወቃል ፡፡ይህንንም ለፌዴሬሽኑ በደብዳቤ አስገብተናል፡፡
ልጆቹም ይህንን አውቀው ለክለቡ ይቅርታ ጠይቀዋል ክለቡ ይቅርታቸውን የመቀበልም ያለመቀበልም መብት አለው፡፡ ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን ከማሳለፉ በፊት እኛን ለማስማማት ምንም አይነት ስራ አልሰራም ይባስ ብሉ ህጉን ሽሯል፡፡ደደቢት የይግባኝ ደብዳቤ ለማስገባት የ3ቀን የግዜ ገደቡን ፌዴሬሽኑ ሳያከብርልን ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡
- ማሰታውቂያ -
የይግባኝ ደብዳቤያችንን ለፌዴሬሽኑ እና ለሚዲያው እንዲበተን አድርገናል ሲሉ አቶ ተስፋዬ የደደቢት ለሀትሪክ ስፖርት ድህረ ገፅ ገልፀዋል፡፡
———————————-
ለደደቢት አግር ኳስ ክለብ የይቅርታ ደብዳቤ ካስገቡተ መካከል ሳምሶን ጥላሁንን በበኩል ከደደቢት የቀረበባቸውን ክስ በተመለከተ ለድህረገፃችን እሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ሳምሶን ጥላሁን:-ለክለቡ የይቅርታ ደብዳቤ አስገብተናል፡፡ሆኖም ክለቡ ይቅርታችንን ሳይቀበለን ከወር በላይ ቆይተናል ፡፡ ለዛም ነው መፍትሄ ለማግኘት ወደ ፈዴሬሽኑ የሄድነው፡፡ሆኖም ለክለቡ የመለቀቂያ ይሰጠን ብለን ስንጠይቅ በሁለት ቀን ውስጥ በድጋሚ ይቀጡ ብለው ነው ደብዳቤ የፃፉብን፡፡
የይቅርታውን ምላሽ ለመስጠት እና የመልቀቂያ ወረቀት ይሰጠን ብለን የጠየቅንበት የደደቢቶች የገዜ ምላሽ አይገናኝም፡፡እንደሚታወቀው ክለቦች የዝውውር እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡ የዝውውር መስኮቱ ሊዘጋብኝ ስለሆነ ይህን እርምጃ ወስደናል፡፡
ፌዴሬሽኑም በሰጠን ፍትሀዊ የሆነ ምላሽ ደስተኞች ነን ሲል ለሀትሪክ ስፖርት ድህረ ገፅ ገልጿል፡፡