የፋሲል ከነማው የፊት መስመር ተጫዋች አማኑኤል ገ/ሚካኤል እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ወደ ሜዳ እንደማይመለስ ክለቡ ይፋ አድርጓል።
በፕሪሚየር ሊጉ 18ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ቡና ከፋሲል ከነማ ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ ላይ ከበረከት አማረ ጋር ተጋጭቶ ጉዳት ያስተናገደው ተጫዋቹ የቀዶ ጥገና አድርጓል።
በዚህም ለቀጣይ ሶስት ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ፋሲል ከነማ አረጋግጧል።
- ማሰታውቂያ -
አማኑኤል ገ/ሚካኤል በውድድር ዓመቱ 14 የሊግ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 4 ግቦችን አስቆጥሯል።