የ2014 ዓ.ም የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በሁለተኝንት ያጠናቀቁት ፋሲል ከነማዎች የነባር ተጫዎቻቸውን ውል በማደስ ላይ ተጠምደው የቆዩ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ መናፍ ዐወልን ቀዳሚ ፈራሚያቸው በማድረግ አስተዋውቀዋል ።
መናፍ ዐወል በተጠናቀቀው የውድድር የባህርዳር ከተማን የኋላ መሰመር በአስተማማኝ ሁኔታ ሲመራ የነበረ ሲሆን ከባህርዳር ቀደም ብሎም በአዳማ ከተማ ተጫውቶ ማሳለፍ ችሏል ።
ከክለብ ቆይታዎች ባለፈም ከ23 አመት በታች እና በዋናው ብሄራዊ ቡድን ማልያ ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል ።
ተጫዋቹ መቀመጫውን በጎንደር ከተማ ባደረገው ክለብ ለሁለት ዓመታት ለመቆየት የሚያስችለውን ፊርማ ያኖረ ሲሆን ወሳኙን ተከላካያቸውን ያሬድ ባየህን ያጡት ፋሲል ከነማዎች ጥሩ ምትክ ያገኙ ይመስላል ።