በተጠናቀቀው የውድድር አመት በሊጉ በ43 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ የቻለዉ ፋሲል ከነማ የአራት ወር ደመወዝ ለተጫዋቾቹ አለመክፈሉን የክለቡ ተጫዋቾች ለሀትሪክ ስፖርት ድህረገጽ ገልጸዋል።
ከወር በፊት የቀድሞውን አሰልጣኙን ዉበቱ አባተ በዋና አሰልጣኝነት መሾም የቻለዉ እና በዝውውር ገበያዉ ላይም በንቃት በመንቀሳቀስ የተለያዩ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ለመቀላቀል እየጣረ የሚገኘዉ ፋሲል ከነማ የአራት ወር ደመወዝ ለነባር ተጫዋቾቹ አለመክፈሉ ሲገለፅ ፤ ነገር ግን ክለቡ በአመቱ መጨረሻ ኮንትራታቸው ለተጠናቀቁ እና የዉጭ ሀገር ዜግነት ላላቸዉ ተጫዋቾች ሙሉ ደመወዛቸዉን በመክፈል ከክለቡ ሲያሰናብታቸዉ ለቀሪ የክለቡ ተጫዋቾች ግን ክለቡ ይህንን አለማድረጉ እንዳሳዘናቸዉ ተጫዋቾቹ ቅሬታቸዉን ለህተሪክ ድህረገጽ አጋርተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ተጫዋቾቹ ቃል የተገባላቸዉን ሶስት የጨዋታ ኢንሴንቲቭም እንዳልተሰጣቸዉ እና የክለቡን የበላይ አመራሮች በተደጋጋሚ ለመጠየቅ ቢሞክሩም ከአመራሮቹ ትንሽ ጠብቁ በሚል ተስፋ አራት ወራት ያህልን ማስቆጠራቸዉን ተናግረዋል።