ከ2012 የዉድድር አመት አንስቶ በፋሲል ከነማ ቤት ቆይታ የነበረዉ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከክለቡ ጋር ከሁለት አመት ከግማሽ በኋላ በስምምነት መለያየቱን ለማረጋገጥ ችለናል።
በ2013 የዉድድር አመት ፋሲል ከነማ በታሪኩ የመጀመሪያውን የሊጉን ዋንጫ ከፍ አድርጎ እንዲያነሳ ማድረግ የቻለዉ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ በዘንድሮው የዉድድር አመት ክለቡ በገባበት የዉጥ ቀዉስ ምክንያት አንድ የፕሪሚየር ሊግ ፣ አንድ የጥሎ ማለፍ እንዲሁም አንድ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን ማሳካት ከቻለበት ፋሲል ከነማ ጋር መለያየቱ ተረጋግጧል። በቀጣይ ፋሲል ከነማ አዲስ አሰልጣኝ እስኪቀጥር ድረስ በምክትል አሰልጣኞቹ እንደሚመራ ለማወቅ ችለናል።