በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ዉድድር ላይ ተሳታፊ የሆኑት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ሁለተኛ ዙር ጨዋታቸውን ዛሬ ያካሂዳሉ።
ጊዮርጊሶች የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸው ከዛንዚባሩ ኬ ኤም ኬ ኤም ጋር በማድረግ በሜዳቸዉም ከሜዳቸዉ ዉጪም በአጠቃላይ 5ለ2 በሆነ ዉጤት በማሸነፍ ለሁለተኛ ዙር ጨዋታ ማለፋቸው ይታወሳል።
ጊዮርጊሶች ዛሬ ላለባቸዉ ጨዋታ 30 የቡድን አባላትን ይዘዉ ወደ ካይሮ የተጓዙ ሲሆን ጨዋታቸዉን ዛሬ ከምሽቱ 2:00 ሰአት በካይሮ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ከአል አሀሊ ጋር የሚያደርጉ ይሆናል።
- ማሰታውቂያ -
በዛሬው ጨዋታ ላይ የግብፅ የፀጥታ ሀይሎች በመፍቀዳቸው 30,ዐዐዐ (ሰላሳ ሺህ) ደጋፊዎች ሜዳ ገብተዉ ጨዋታዉን ይታደማሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊሶች ሁለተኛውን ጨዋታቸዉንም እዛው ለመጫወት በመወሰናቸዉ የፍለፊታችን አርብ መስከረም 18/2016 ዓ.ም በካይሮ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ከአል አሀሊ ጋር የሚያደርጉ ይሆናል።