በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመራው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሶስት ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ መቀላቀሉን ይፋ አድርጓል።
ባለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት በኢትዮጵያ ቡና ቤት ቆይታ ያደረገው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ፊርማውን አኑሯል።
አብዱልሀፊዝ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ከመዘዋወሩ አስቀድሞ በሰበታ ከተማ ድንቅ እንቅስቃሴ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ተሰልፎ መጫወቱ ይታወቃል።
የቀድሞው የድሬዳዋ ፖሊስ ፣ ወልዋሎ አዲግራት ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና ባህርዳር ከተማ ተጫዋች አፈወርቅ ሀይሉ ፈረሰኞቹን የተቀላቀለው ሌላኛው ተጫዋች ነው።
- ማሰታውቂያ -
የክለቡ የሀያ አመት በታች ቡድን አምበል የነበረው ፉአድ አብደላም በይፋ ፊርማውን ያኖረው ሶስተኛ ተጫዋች ነው።
ሶስቱም ተጫዋቾች እያንዳንዳቸው ለሁለት አመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያቆያቸውን ውል ተፈራርመዋል።