20ኛው የ 2013 ቶታል ታላቁ ሩጫ በዛሬው ዕለት በደማቅ ሁኔታ ተካሂዶ ሊጠናቀቅ ችሏል ።
በመርሐ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተገኝተው ባስጀመሩት መርሀ ግብ የወንዶች እና ሴቶች ውድድር ሲካሄድ በሴቶች ዘርፍ ፅጌ ገብረሰላማ ለተከታታይ አመት ያሸነፈችበትን ውጤት በዛሬው እለት አስመዝግባለች ።
- ማሰታውቂያ -
አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ 32:32.433 በመግባት ቀዳሚ መሆን ስትችል የንግድ ባንኳ አትሌት መድህን ገ/ስላሴ እና የመከላከያዋ አባይነሽ አየሌ ተከታዩን ደረጃ ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል ።
በወንዶች በተደረገ ውድድር አቤ ጋሻው 28:19.105 በሆነ ደቂቃ በመግባት ውድድሩን በባላይነት ሲያጠናቅቅ ታደሰ ወርቁ እና ምሌሳ መንገሻ በመከታተል በመግባት ውድድራቸው አጠናቀዋል ።
ውድድሩን በአንደኝነት ያጠናቀቁ አትሌቶች ዳጎስ ያለ ሽልማት ሲበረከትላቸው የ አንድ መቶ ሺህ ብር ሽልማት መሸለማቸው ተገልጿል ።
የኮቪድ ጥብቅ ፕሮቶኮልን ተከትሎ የተካሄደው የቶታል የታላቁ ሩጫ እንዳለፈፉት ዓመታት ሁሉ በደማቅ ሁኔታ ሲጠናቀቅ በጎዳና ላይ ሩጫ 12,500 ተሳታፊዎችን በማሳተፍ የዘንድሮውን የውድድር ዓመት በደመቀ መልኩ አካሂዶ አጠናቋል ።