በዘንድሮው የዉድድር አመት በጠንካራ ተፎካካሪነት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በአራተኛ ደረጃ ያጠናቀቀው ሀዲያ ሆሳዕና ወጣቱን የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትን በዋና አሰልጣኝነት ተቀጥረዋል።
እንደሚታወቀዉ ከአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጋር ባለመስማማት ከቱያዩ በኋላ አሰልጣኝ እያሱ መርሐፅድቅን በጊዜያዊነት አሰልጣኝ አድርጎ በመሾም የዉድድር ዓመቱን ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።
በዉድድር አመቱም ተጫዋቾቹ ከክለቡ አመራሮች ጋር ባለመግባባት እና መስማማት ባለመቻላቸው ምክንያት የሊጉን የመጨረሻ ጨዋታዎች በታዳጊዎች ለመጫወት ተገደዉ እንደነበርም ይታወሳል። እንደዛም ሆኖ ግን የዉድድር አመቱን እንደ አጀማመራቸው ባይሆንም በጥሩ ዉጤት ለማጠናቀቅ ችለዋል።
በ2014 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ጥሩ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቀጠል ዘንድሮ በሀዋሳ ከተማ ያሳለፈዉን አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትን በሁለት አመት ኮንትራት መሾማቸውም ተሰምቷል።