*…. አመራሮቹ አንድ አካዳሚን ዛሬ ጎብኝተዋል….
የሀድያ ሆሳዕና እግርኳስ ክለብን በፋይናንስ ለማጠናከር ያለመው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በጆሃንስበርግ ከተማ ተደረገ።
22 ተጨዋቾችን ጨምሮ 37 የልኡካን ቡድን በሁለት ጊዜ በረራ ትላንት ደቡብ አፍሪካ መዲና ጆሀንስበርግ መግባቱ የሚታወቅ ሲሆን በርካታ የክለቡ ደጋፊዎች በተገኙበት የክለቡን የፋይናንስ አቅም በሚያጠናክር መልኩ የገቢ ማሰባሰቢያ መካሄዱ ታውቋል። በቀጣይ ቀናት አጠቃላይ ሂደቱን የክለቡ አመራሮች መግለጫ እንደሚሰጡበት ይጠበቃል።
- ማሰታውቂያ -
ጉዞውን ያስተባበረው የፊፋ ማች ኤጀንት ኢንጂነር ፍጹም አድነው በበኩሉ በተለይ ለሀትሪክ ድረገጽ እንደገለጸው ቡድኑ ዛሬ ልምምድ ያደረገ ሲሆን ከክለቡ አመራሮች ጋር በመሆን ጆሀንስበርግ የሚገኝ አካዳሚ መጎብኘታቸውን አስረድቷል። ቡድኑ በቀጣይ እሁድም ከጂዲ አር ስታርስ ጋር ለሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ እየተዘጋጀ መሆኑን ኢንጂየር ፍጹም ለሀትሪክ ድረገጽ ተናግሯል።