…ሀድያ ሆሳዕና በሶስት ቀን ውስጥ
የ15ቱን ተጨዋቾች ደመወዝ እከፍላለሁ አለ
ከደረቅ ቼክ ተያይዞ በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉት የሀድያ ሆሳዕና የፋይናንስ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ በዋስ ተለቀቁ።
ላለፉት 21 ቀናት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበሩት አቶ ዛሬ የዋስ መብታቸው ተከብሮ ተለቀዋል።
በሌላ በኩል ሀድያ ሆሳዕና ከተከሰሰበት ክስ ነፃ ለመውጣት ከተጨዋቾቹና ጠበቃቸው አቶ ብርሃኑ በጋሻው ጋር ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል።
ዛሬ በኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ፕሬዝዳንቱ አቶ ኢሳያስ ጅራና የሀድያ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ማቲዮስ በተገኙበት በተካሄደው ድርድር ክለቡ በሶስት ቀን ውስጥ ደመወዛቸውን ለመክፈልና ቼኩን በተመለከተም በየግል ተወያይቶ ስምምነት ላይ ለመድረስ መስማማታቸው ታውቋል።
- ማሰታውቂያ -
ክለቡ “ክፍያውን የምንፈጽመው ግን በፔሮል ስለሆነ ሆሳዕና መጥተው ያለባቸውን ትጥቅ መልሰው ነው” ቢልም በተጨዋቾቹና ጠበቃቸው ተቃውሞ ገጥሞታል። “እዚያ ድረስ ለመጓዝ አንተማመንም ምን እንደሚገጥመንም አናውቅም” በማለት ሌላ ጊዜ በባንክ ሲከፈለን ቆይቶ ዛሬስ ለምን በፔሮል ይሆናል? በማለት እንደማይቀበሉት ገልጸዋል።
ሀድያ ሆሳዕና አዲስ አሰልጣኝ በማድረግ ሙሉጌታ ምህረትን ቀጥሮ ዝውውር ቢያደርግም እስካሁን አለመጽደቁ ታውቋል።