በሊጉ የመዝጊያ ጨዋታ በ30ኛዉ ሳምንት ከሲዳማ ቡና ጋር ጨዋታቸዉን እንዲያደርጉ መርሐግብር የወጣላቸዉ ሀድያ ሆሳዕናዎች ከደሞዝ እና ጥቅማጥቅሞች ጋር ተያይዞ ልምምድ ማቆማቸዉን ሰምተናል።
የሚያዚያ ፣ ግንቦት እና የሰኔ ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም ያሉት ተጫዋቹ ከዚህ በተጨማሪም የአምስት ጨዋታ ኢንሴንቲቭ እስከአሁን ድረስ ሊከፈለን ባለመቻሉ ምክንያት በተደጋጋሚ ቅሬታችንን ለሚመለከታቸዉ የክለቡ አመራሮች ብናቀርብም ይህ ነዉ የሚባል ምላሽ ባለማግኘታችን ምክንያት ከዛሬ ሰኔ 22 ጀምሮ ልምምድ አቁመናል ሲሉ አቋማቸዉን አሳዉቀዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም የፊታችን ቅዳሜ በሰላሳኛዉ ሳምንት የሊጉ መርሐግብር ግብር ከሲዳማ ቡና ጋር የሚደረገዉን ጨዋታ እንደማይጫወቱ ተጫዋጮቹ አስረግጠው ተናግረዋል።
ይሄንን ጉዳይ በተመለከተም የክለቡ አመራሮች የተጫዋቾቹ ቅሬታ መኖሩን አምነዉ ነገር ግን ክፍያዉን ለመፈፀም አዲሱ የበጀት አመት እስኪፀድቅ ድረስ መጠበቅ እንዳለባቸው ገልፀዋል።
- ማሰታውቂያ -
ዉድ የሀትሪክ ድህረገፅ አንባቢያን በዚህ ጉዳይ ላይ አዳዲስ መረጃዎች የሚኖሩ ከሆነ እየተከታተልን የምናደርስ ይሆናል።