*…. የፊፋ ማች ኤጀንት ፍጹም አድነው ለትግራይ ክለቦች ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባ….
ሶስቱ የትግራይ ክለቦችን ወደ ውጪ ሃገር ወስዶ ገቢ ማሰባሰቢያ ለማድረግ መዘጋጀቱን የፊፋ ማች ኤጀንት ፍጹም አድነው ተናገረ።
በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው የትግራይ ክለቦችን እንታደግ ዘመቻ የመዝጊያ መርሃግብር ላይ የተገኘው ፍጹም ” ሶስቱም ክለቦች / መቀለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ አዲግራትና ስዑል ሽረ/ ወደ ሶስት ሀገራት በመውሰድ ተከፍሏቸው የወዳጅነት ጨዋታ እንዲጫወቱና እዚያው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እንዲዘጋጅ ለማድረግ መወሰኑን ገልጾ ከአንድ ትጥቅ አምራች ኩባንያ ጋር በመነጋገር ለሶስቱም ደረጃውን የጠበቀ ማሊያ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ገልጿል።
የፊፋ ማች ኤጀንት ፍጹም ሀድያ ሆሳዕና ከአንድ የደቡብ አፍሪካ ክለብ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንዲያደርጉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጾ የፊታችን ረቡዕ ከቀኑ 8 ሰአት 22 በሚገኘው የኒያላ ኢንሹራንስ በጉዞው ዙሪያ ከክለቡ አመራሮች ጋር መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል። ሙሉ የሀድያ ሆሳዕና ቡድን የፊታችን ሀሙስ ወደ ጆበርግ እንደሚያቀኑም ይጠበቃል።
- ማሰታውቂያ -
የፊፋ ማች ኤጀንት ፍጹም አድነው በቅርቡ ሸገር ደርቢን በዱባይ እንዲካሄድ ማድረጉ ይታወሳል።