በተጠናቀቀዉ የውድድር አመት በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ እየተመራ በፕሪምየር ሊጉ 41 ነጥቦች በመሰብሰብ ስምንተኛ ደረጃን ይዘዉ ማጠናቀቅ የቻሉት ነበሮቹ ፤ ለቀጣዩ የውድድር አመት ተጠናክረዉ ለመቅረብ ይረዳቸዉ ዘንድ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ መቀላቀል ጀምረዋል።
በዚህም እስከ አሁን የተከላካዮቹን ከድር ኩልባሊ እና ሳሙኤል እንዲሁም መለሰ ሚሻሞ ዉል ያደሱት ሀድያዎች አሁን ደግሞ ያለፈዉን የውድድር ዘመን በሀዋሳ ከተማ ቤት ማሳለፍ የቻለዉን የፊት መስመር ተጫዋቹን እዮብ አለማየሁ በሁለት አመት የኮንትራት ውል ወደ ስብስባቸዉ መቀላቀል ችለዋል።