በዘንድሮው የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ድንቅ ጅማሮን ማድረግ የቻሉት ሀድያ ሆሳዕናዎች በአዳዲስ ተጫዋቾች ቡድናቸውን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ ።
ዛሬ ከሰዓት ከ ክለቡ በተሰማ መረጃ ነብሮቹ ያለፉትን በርካታ አመታት በ ግብፅ ሊግ ጥሩ ጊዜን ያሳለፈው የመስመር ተጫዋች ኡመድ ኡኩሪ ማስፈረማቸው ይፋ ሆኗል ።
የኡመድ ኡክሪ ቡድኑን መቀላቀል በተለይም ከቀናት በፊት ወደ ሀገሩ በግል ምክንያት ለተመለሰው ሳሊፍ ፎፎና ቦታ ትልቅ ሽፋን እንደሚሰጥ ይታመናል ።
ኡመድ ኡክሪ አዳማ ከተማን ጨምሮ ስሙ ከተለያዩ የሊጉ ክለቦች ጋር ቢያያዝም የአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ስብስብ ምርጫው አድርጓል ።