በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ እየተመሩ የዝዉዉር መስኮቱ ገና ከመከፈቱ ከወዲሁ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ እየቀላቀሉ የሚገኙት ሀዋሳ ከተማዎች አሁን ደግሞ ሁለገቡን ተጫዋች ሙጅብ ቃሲምን ማስፈረማቸዉ ተረጋግጧል።
ከዚህ ቀደም ለሲዳማ ቡና ፣ ሀዋሳ ከተማ እና አዳማ ከተማ እንዲሁም ያለፉትን አምስት ያህል አመታት ለፋሲል ከነማ መጫወት የቻለዉ ተጫዋቹ በዛሬዉ ዕለት ደግሞ ቀጣዮቹን ሁለት አመታት ለሀዋሳ ከተማ ለመጫት ፊርማዉን ማኖሩ ታዉቋል።
በኢትዮጵያ እግርኳስ ዉስጥ የተለያዩ ቦታዎች ላይ መጫወት ከሚችሉ እና ዉጤታማ ናቸዉ ከሚባሉ ጥቂት ተጫዋቾች መካከል ዋነኛ ተጠቃሽ የሆነዉ ሙጅብ ቃሲም ለሀይቆቹ የተለይ ጥንካሬን ሊሰጥ እንደሚችልም ከወዲሁ ይጠበቃል።