በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ እየተመሩ በዝዉዉር ገበያዉ በንቃት በመሳተፍ ስድስት ያህል አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ መቀላቀል የቻሉት ሀዋሳ ከተማዎች አሁን ደግሞ ሰባተኛ ፈራሚ በማድረግ ተከላካዩን ሰለሞን ወዴሳን ወደ ቡድናቸዉ ቀላቅለዋል።
ከዚህ ቀደም ለሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ሙድህን እንዲሁም ያለፉትን ሶስት አመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት ማሳለፍ የቻለዉ ተከላካዩ ሁለት አመት በሚቆይ ዉል ለሀዋሳ ከተማ መፈረሙ ተረጋግጧል።