ከሰሞኑ በዝውውሩ መስኮቱ በንቃት በመሳተፍ ላይ ያለው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በዛሬው ዕለት ወንድማገኝ ማዕረግን አስፈርሟል ።
ተጫዋቹ ከሀዋሳ ከተማ ታዳጊ ወጥቶ በዋናው ቡድንም ተጫውቶ ማሳለፍ የቻለ ሲሆን ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለተኛ ክለቡ ሆኗል ።
ወንደማገኝ በ2015 ወደ ሊጉ በተመለሰው ክለብ ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት ለመጫወትም ፊርማውን አኑሯል ።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከዚህ ቀደም ሰለሞን ደምሴ ፤ ፍቅሩ ወዴሳ ፤ ጌቱ ሀይለማርያም ፤ ሀይሌ ገብረትንሣኤ ፤ ታፈሰ ሰርካ እና ተስፋዬ በቀለን ማስፈረማቸው ይታወሳል ።