ከአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ጋር ከተለያዩ በኋላ አሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን በዋና አሰልጣኝነት የተቀጠረዉ ሀዋሳ ከተማ ተከላካይ መስመር ተጫዋች አስፈርሟል።
አሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን በሁለት ዓመት የውል ስምምት በቅርቡ የቀጠረው ሀዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት ደግሞ ወደ ዝዉዉሩ ፊታቸውን በማዞር ተከላካዩን ፀጋሰዉ ድማሙ ማስፈረማቸዉ ተረጋግጧል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በዘንድሮዉ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ለክለቡ ሀድያ ሆሳዕና በተሰለፈባቸዉ ጨዋታዎች በሙሉ ምርጥ ብቃቱን በማሳየት በጥሩ አቋም ሊጉን ያጠናቀቀወዉ ተጫዋቹ ረዘም ያሉ አመታትን ካሳለፈበት ሀድያ ሆሳዕና በዛሬዉ ዕለት ለሀዋሳ ከተማ ፊርማዉን አኑሯል።