በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ እየተመሩ ወደ ዝዉዉር ገበያዉ ጎራ በማለት የተለያዩ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ የሚገኙት ሀዋሳ ከተማዎች ከዚህ በፊት ተከላካዩን ፀጋሰዉ ድማሙ እና አማካዩን በቃሉ ገነነ ማስፈረማቸዉ ይታወሳል።
አሁን ደግሞ የክለቡን ወሳኝ ተጫዋች የሆነዉን ጋናዊውን ተከላካይ ላዉረንስ ላርቴን ለተጨማሪ አመት በክለባቸዉ ለማቆየት መስማማታቸው ታዉቋል።
በ2009 የዉድድር አመት ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ ወጥ በሚባል አቋም ክለቡን ሲያገለግል የቆየዉ የመሀል ተከላካዩ አሁን ደግሞ ለተጨማሪ አመታት በሀይቆቹ ቤት የሚያቆየውን የስምምነት ዉል መፈራረሙ ተረጋግጧል።