ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል የመሐል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ከ አንድ ወር በኋላ በሚካሄደው የሀገራት የ 2021 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ እንዲመራ መመረጡ ታውቋል ።
ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የትላልቆቹን ሀገራት ጋና እና ደቡብ አፍሪካ የሚገናኙበትን ግዙፍ ጨዋታ እንደሚመራ ይጠበቃል ።
የጋና ብሔራዊ ቡድን ከ ባፋና ባፋናዎቹ ጋር መጋቢት 16 በ ጆሀንስበርግ ጋር ትልቅ መርሐ ግብራቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል ።
ከኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በተጨማሪም ክንዴ ሙሴ እና ተመስገን ሳሙኤል ይህን ጨዋታ ከ ባምላክ ጋር በረዳት ዳኝነት እንደሚመሩ ለማወቅ ተችሏል ።
- ማሰታውቂያ -
ይህን ጨዋታ በአራተኛ ዳኝነት ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ብሩክ የማነብርሀን ሆነው መሾማቸው ለማወቅ ችለናል ።