ከሰበታ ከተማ ጋር ውሉን የጨረሰው ዳዊት እስጢፋኖናን የአሸናፊ በቀለን ጅማ አባጅፋርን ለአንድ አመት ተቀላቀለ።
አሁን በወጣ መረጃ ዳዊት አስጢፋኖስ በኢትዮዽያ ቡናና ሰበታ ከተማን አብሮት የተጫወተውን መስኡድ መሃመድን የሚያገኘው ይሆናል።
በማራኪ አጨዋወቱ የሚታወቀው ዳዊት አስጢፋኖስ ዘንድሮ ጥሩ እንቅስቃሴ ማሳየቱ ቢታወቅም ሰበታ ከተማና አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ውሉን ሳያድሱለት ቢቀርም ጅማ አባጅፋር ለአንድ አመት በመሃል ሜዳው ላይ እንዲታይ ፈቅዷል።
ጅማ አባጅፋር ራሱን እያጠናከረ ሲሆን ከደመወዝ ጋር ተያይዞ የሚነሳውን ስሙን በማራኪ አጨዋወት ያስረሳ ይሆን የሚለው የስፖርት ቤተሰቡ ጥያቄ ሆኗል።