የኦሮሚያ ክልል ስፖርት ኮሚሽን የጅማ አባጅፋርን ጉዳይ በጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ስር ያደረገ ይመስላል…ቡድኑን ለማትረፍ ባለ ልምዱን አሰልጣኝ ጸጋዬ ኪዳነ ማርያምን ለመቅጠር ከጫፍ መድረሱ እየተነገረ ነው።
የክለቡ አመራሮች ከስፖርት ኮሚሽኑ ሰዎች ጋር በመሆን አሰልጣኙን ለማግባባትና ለመቅጠር የመጨረሻው ድርድር እየተካሄደ መሆኑ ከታማኝ ምንጭ የተገኘ መረጃ ያስረዳል።
አሰልጣኙ በባህርዳር ስታዲየም ጅማ አባጅፋርን የሚመራ ሲሆን ከሲዳማ ቡና ከአሰልጣኝ ገ/መድህን ኃይሌ በቀጣይ ከሀዲያ ሆሳዕና ከአሰልጣኝ አሽናፊ በቀለ ጋር የሚፋጠጥ ይሆናል።
ጅማ አባጅፋር በ4ነጥብና 13 የግብ ዕዳ 13ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን የአሰልጣኝ ጸጋዬ ትልቁ የቤት ስራ ቡድኑን ከወራጅ ቀጠና ማውጣትና ተፎካካሪ ማድረግ ይሆናል ተብሎ ይጠብቃል።