በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ከዉድድሩ እንዲሁም ከሚደረጉ ጨዋታዎች ፉክክር ባሻገር ሁልጊዜም በየአመቱ አብሮ የሚነሳዉ የክለቦች እና የተጫዋቾች የደመወዝ ዉዝግብ ሲሆን በዚህኛው አመትም አጠቃላይ ካሉት 16 ክለቦች መካከል አስራ አንዱ ክለቦች ደመወዝ በአግባቡ ለተጫዋቾቻቸው መክፈል የማይችሉ እንደሆኑ ከሊግ ካምፓኒዉ አመራሮች መካከል ባለፈዉ ሳምንት በአንድ ስብሰባ ላይ ሲገለፅ ተስተውሏል።
አሁን ደንሞ ጅማ አባጅፋር ስፖርት ክለብ ለ25 ተጫዋቾች ባልከፈለዉ የሁለት እና የሶስት ወር ደመወዝ ምክንያት ከተጫዋቾቹ ዘንድ ቅሬታ እየቀረበበት ይገኛል። ለዚህም ማሳያነት ጅማ አባጅፋር ስፖርት ክለብ በአሁኑ ሰዓት ለ5 ተጫዋቾች የሶስት ወር እንዲሁም ለ20 ተጫዋቾች ደግሞ የሁለት ወር ደመወዝ እስከ አሁን ድረስ መክፈል አለመቻሉ ተገልጿል።
በተደጋጋሚ የክለቡን አመራሮች ቢጠይቁም ትንሽ ጠብቁ ይገባላችኋል ከማለት ዉጭ ይሄ ነዉ የሚባል መፍትሄ ባለማግኘታቸዉ ምክንያት ወደ ክስ ሊያመሩ እንደሆነም ተጫዋቾቹ ገልፀዋል።