የትግራይ ክልል ክለቦች በ2014 የዉድድር አመት አለመሳተፋቸውን ተከትሎ በሊጉ ዳግም የመወዳደር የሚያስችላቸውን ዕድል ያገኙት ጅማ አባጅፋሮች ከአሠልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ጋር ከተለያዩ በኋላ ፊታቸውን ወደ አሰልጣኝ ቅጥር በማዞር የቀድሞዉን የሀድያ ሆሳዕና አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን መቅጠራቸዉ ታዉቋል።
ከበርካታ አሰልጣኞች ጋር ስሙ ሲያያዝ የቆየዉ ጅማ አባጅፋር በመጨረሻም የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ መከላከያ፣ ሲዳማ ቡና፣ አዳማ ከተማ ፣ ወላይታ ድቻ እና ሀዲያ ሆሳዕና አሠልጣኝ የነበሩት አሸናፊ በቀለን ማስፈረማቸዉ ተረጋግጧል።
ዘግይተዉም ቢሆን አሰልጣኝ መቅጠር የቻሉት ጅማዎች በቀጣይነት ደግሞ ወደ ዝዉዉሩ በመግባት ተጫዋቾችን እንደሚያስፈርሙም ይጠበቃል።