በአትሌቲክሱ ዘርፍ ኢትዮጵያን ካስጠሩ አትሌቶች መካከል ግምባር ቀደሙ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በአርሲ ዩኒቨርስቲ አማካኝነት ለሰራቸዉ ስራዎች እና ሀገሩን በአለም መድረክ በማስጠራቱ የክብር ዶክትሬት ተበርክቶለታል።
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለሀገሩ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ሶስት ወርቆችን ያስገኘ ሲሆን በአገር አቋራጭ ዉድድርም አምስት ጊዜ ወርቅ በማምጣት የሀገሩን ስም አስጠርቷል እንዲሁም በግል ዉድድሮች በ 10,000 ሜትር፣ በ 5000 ሜትር እንዲሁም በማራቶን ዉድድሮች በርካታ ክብሮችን ማግኘት የቻለ አትሌት ነዉ።
ከሩጫዉ በተጨማሪ በሆቴል ኢንቨስትመንት በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች የተሰማራ ሲሆን ለሀገሩ ባበረከተዉ አስተዋፆ ከአርሲ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ተሰጦታል።