የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀው ” የከንቲባ ካፕ” በቅርቡ ሊካሄድ መሆኑን የአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ፌዴሬሽኑ እንደገለጸው ውድድሩ በሁለቱም ጾታዎች ከ8-12 በሚደርሱ የከፍተኛና የአንደኛ ሊግ ክለቦች መሃል በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በቅርቡ እንደሚደረግ ገልጿል።
ከፌዴሬሽኑ በተገኘው መረጃ ስለ ውድድሩ የተሟላ መረጃ እንዲኖር በኤሊያና ሆቴል የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 8″ ሰዓት ጋዜጣዊ መግለጫ የተዘጋጀ ሲሆን ከመግለጫው ጎን ለጎንም የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት እንደሚኖር ፌዴሬሽኑ አስረድቷል።